tg-me.com/nibab_lehiwot/175
Last Update:
የእኔ ታሪክ ምዕራፍ -2
ክፍል -12
ቪ እባክሽ እሽ በይኝ .....አትወጅኝም እንዴ አሌፍ እንደተንበረከከ መለመኑን ቀጥሏል። ቪቪያን በእሽ እና እምቢ ውስጥ ግራ ገብቷት ቆማለች። በአባቷ እና በአሌፍ መሃል .....ድንገት አብራው መሆን እንደምትችል የነገራት ትዝ አላት........ እና ልትናገር ከንፈሮቿን ማንቀሳቀስ ስትጀምር ....እ....ማቲ መጥቶ አቋረጣቸው። ቪቪ አባባ አሌፍ ካልመጣ አላወራም ብሏል በጣም እየደከመ ነው እባክሽ እንፍጠን ስለምታወሩት ነገር በኋላ አውሩ አላት ፍጥን ፍጥን እያለ። አሌፍ ተነስ እንሂድ አለችው ከተንበረከከበት እጁን ጎትታ እያስነሳችው። (አሌፍ በዛ ቅፅበት ማቲያስን ጠላው።) ሶስቱም ተያይዘው ወደ ሆስፒታል ጉዞ ጀመሩ።
ሆስፒታል ሲደርሱ አሌፍ ብቻ ወደውስጥ ገብቶ ሌሎቹ ውጭ ጠበቁት። አባባ ደህና ኖት አለ የፊቱ መገርጣት እያስደነገጠው። ደ......ደህና ነኝ ልጄ... ለ ...ምን ነበር ልታናግረኝ የፈለግከው? ኧረ እሱ ቀስ ብሎ ይደርሳል መጀመሪያ ጤና ይበልጣልኮ
ልጄ ለሽማግሌ ነገ የሚባል ጊዜ የለውም አሁን ን...ገረኝ የሕዝቅኤል ድምፅ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። እ ስለ ቪቪያን እና ስለ እኔ ላናግርክ ነበር ። ብዙ አሳሳቢ አይደለም ቀስ ብሎ ይደርሳል አለ አንገቱን እያቀረቀረ። እምምምም እስኪ ለ እናትህ ደውልና አገናኘኝ አለ ሕዝቅኤል ውስጡ እየተጨነቀ። አሌፍ የሕዝቅኤል ሁኔታ ግራ ቢያጋባውም መጥፎ ነገር እንደማያደርግ በሙሉ ልቡ ስለሚያምነው እና ከምንም በላይ ስለሚያከብረው እሽ ብሎ ያዘዘውን አደረገ። ራቢያ አሶስት ጥሪ በኋላ ስልኩን አነሳችው ።እማየ አላት እንደሁሌው ሰሚሬ እንዴት ዋልክ ልጄ ዛሬ ሳናወራ ዋልንኮ ደህና ነህ አለች በስስት አነጋገር። ደህና ነኝ እማ ትንሽ ስላልተመቸኝ ነው የ ቪቪያን አባት ሊያናግርሽ ይፈልጋል አዋሪው ብሎ ስልኩን ሰጣው። ራቢያ ሰውየውን ባታውቀውም ደነገጠች እሷም የቪቪያንን እና የ ልጇን አንድ ላይ መሆን አጥብቀው ከሚቃወሙት ውስጥ ናት። ሰውየው ምን ሊለኝ ይሆን አለች በውስጧ። ሰ...ሰላም ለ አንቺ....አለ ሕዝቅኤል የልብ ምቱ እየፈጠነ። ራቢያ በቁሟ ደረቀች። ሔሎ ሔሎ...ራ .....ሊጨርሰው አለና መልሶ ዋጠው። ሕዝቄ......በህይወት አለህ? እንባ ተናነቃት..... እንደምንም ራሷን እየታገለች.....አንተ ነህ ሕዝቄ.....እውነት አንተ ነህ? አወ እኔ ነኝ ደህና እንደሆንሽ ተስፋ አደርጋለሁ። "ልጆቻችንም ሊጋቡ ነው እንኳን ደስ አለሽ ወይዘሮ ራቢያ" ቅስሙ ስብር ብሎ ነበር ይሄንን የተናገራት ምን ለማለት እንደፈለገ በደምብ ገብቷታል። የእርሷም ውስጥ ስብር አለ .... ምናለ ያኔ ባስተዋውቀው ኖሮ ወይ ራቢያ በቃ ችግር አያጣሽም አይደል ወይ ጣጣ ቻው አቶ ሕዝቅኤል ብላ ስልኩን ዘጋች።
ለስንት አመታት ሙሉ ድምፁን ያጠፋው ሕዝቅኤልን ከብዙ ጊዜ ጥበቃ እና ሀዘን በኋላ እንደሞተ ደምድማ ሀዘኗን አምና ተቀብላው ነበር። ድንገት ግን ሕዝቅኤል መጣ ያውም የሴት ልጅ አባት ሆኖ ለዛውም ደሞ ልጆቻቸው ጭራሽ ሊጋቡ ነው። ራቢያ ራሷን መቆጣጠር አቅቷት ወንበሩን ተደግፋ ማልቀስ ጀመረች። ለምን ? ለምን ይሄ ሁሉ.......
ትተዋወቃላችሁ እንዴ አለ አሌፍ ንግግራቸው ገርሞት .....አወ አሁን አወቅኳት ልጆች እያለን አንድ ላይ ነበር የተማርነው በጣም ጎበዝ ነበረች ይገርምሃል አለው። አሌፍ ግን ደስ የማይል ስሜት ተሰማው እናቱ ከዚህ በላይ ትልቅ ደረጃ መድረስ የምትችል ጠንካራ ሴት እንደሆነች ያውቃል......ባትወልድ ኖሮ!!!!
ሕዝቅኤል ሊሞት እንደሆነ እየተሰማው ስለሆነ ምንም ጊዜ ማጥፋት አልፈለገም።ከዚህ በኋላ ዝም በማለት የማሳልፈው ጊዜ የለኝም አለ በውስጡ።
አሌፍ አባትህ ግን ስለ አንተ ምንም ነገር ነግሮህ አያውቅም?
አልገባኝም ምን አይነት ነገር አለ ግራ እየተጋባ .....
ታሪካቸውን አባትህ እና እናትህ እንዴት እንደተገናኙ አንተ እንዴት እንደ ተወለድክ ?
አይ አባቴ ለዛ ጊዜ አልነበረውም ባይሆን እናቴ ግን ነግራኛለች። አለ...
እንዴት ነበር የተወለድከው?
ይቀጥላል............
@nibab_lehiwot
BY ሕይወትን - በገፅ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/nibab_lehiwot/175